- May 18, 2025
- Posted by: meftihe
- Categories: Announcement, notice
No Comments
የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ
በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013፣ አንቀጽ 366(1) ፣ 367(1) ፣ 370 እና 393(1) እንዲሁም በማኅበሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 17 መሠረት የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤዎች ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሳርቤት በሚገኘው ኢገስት አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባዔዎቹ ላይ እንድትገኙልን የማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል፡፡
- ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
- የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ፤ መፍትሔ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ፤ አዲስ አበባ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ 04፤ የቤት ቁጥር 003፤ የአክሲዮን ማኅበሩ ድረ-ገጽ www.meftihemicrofinance.com
- የአክሲዮን ማኅበሩ አይነት፡- በማይክሮፋይናንስ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማኅበር፤
- የማኅበሩ የምዝገባ ቁጥር፡- MT/AA/3/0056814/2016
- የማኅበሩ የተፈረመ ካፒታል፡- 87,103,000.00(ሰማንያ ሰባት ሚሊዮን አንድ መቶ ሶስት ሺህ) ብር፤
- የማኅበሩ የተከፈለ ካፒታል፤ 60,603,000.00 (ስልሳ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሶስት ሺህ) ብር
- የ2ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም የተከናወኑ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2024/25 የዳይሬክተሮች ቦርድን ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2024/25 የውጪ ኦዲተሮችን ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
- እ.አ.አ የ2025/26 የበጀት አመት የዳይሬክተሮች ቦርድ የስብሰባ አበልን በሚመለከት በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፤
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማከናወን፤
- የ2ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- የማኅበሩን የመመስረቻ ጽሑፍ ለማሻሻል በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- የማኅበሩን የተከፈለ ካፒታል ለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
- ማሳሰቢያ
- በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ከሆነ ከጉባኤው ሦስት (3) ቀናት በፊት ሳር ቤት በሚገኘው የማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ በግንባር ቀርበው ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን የያዙ ተወካይ በዕለቱ በጉባኤው ቦታ የሰነዱን ዋናውን እና አንድ ፎቶ ኮፒ ይዘው እንዲቀርቡ በማድረግ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ባለአክሲዮኖችም ሆኑ ወኪሎች ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤ፋይዳ መታወቂያ፤ፓስፖርት ወይንም መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
- እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሃገር ዜግነት ያላችሁ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት(ቢጫ ካርድ)ይዛችሁ መቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ባለአክሲዮኖች ወደ ስብሰባው ስትመጡ የፋይዳ መታወቂያችሁንና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /Tin/ ዋናውንና ኮፒውን ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡
መፍትሔ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ