
በአክሲዮን ማህበራችን 1ኛ መደበኛ እና 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ፤ ክፍያ ያልተፈጸመባቸውን አክሲዮኖች በተመለከተ ተቋሙን በሚጠቅም መልኩ እና በንግድ ህጉ በተቀመጠው መሰረት ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ጠቅላላ ጉባኤው ለቦርዱ ውክልና መስጠቱ ይታወሳል፡፡
ባለአክሲዮኖችም ክፍያቸውን አጠቃለው እንዲከፍሉ የተቀመጠው የሁለት ወር ቀነ ገደብ የተጠቃለለ ሲሆን በተቀመጠው ግዜ ውስጥም ክፍያቸውን አጠቃልለው የከፈሉት ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው፡:
ከዚህም የተነሳ የዳይሬክተሮች ቦርድ በጉባኤው በተሰጠው ስልጣን መሰረት ክፍያ ያልተፈጸመባቸውን አክሲዮኖች ለሌሎች ከማስተላለፉ በፊት በአጠቃላይ ሂደቱ ላይ ከባለአክሲዮኖቻችን ጋር በአካል እና በበይነ መረብ (Zoom Meeting) መወያት አስፈልጎናል፡፡ ስለሆነም በቅርቡ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ ስለምንጠራ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ እንጠይቃለን፡፡
የመፍትሔ ማይክሮፋይናነስ የዳይሬክተሮች ቦርድ